በሀረሪ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር
ዳይሬክቶሬት በመንግስት ግዥ አፈጻጸምና አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
የስልጠናው አላማ ሰልጣኞች በመንግስት ግዥ አዋጅና መመሪያ ላይ በቂ እውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት እንዲኖራቸው በማድረግ በቀጣይ በግዥ አፈጻጸም ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ ራሳቸውን ችለው ግዥውን እንዲያከናውኑ ማብቃት ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ ተመላክቷል።
ለተከታታይ ቀናት ሶስት በቆየው በዚህ ስልጠና ስለ መንግስት ግዢ ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ አፈፃፀም ባህሪያት፣ የግዢ ጨረታ አወጣጥ፣ ስለ ግዢ መመሪያዎች አጠቃቀምና አተገባበር በሚሉ ይዘቶች ያተኮረ እንደሆነ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የግዥ ከፍተኛ ባለሞያ የሆኑት ወ/ሮ ሩሚያ አሊዪ ገልፀዋል።
ሰልጣኞች በግዥ አፈፃፀም መመሪያው ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ በግዥ መርሆዎች ስርዓቶች ላይ ውጤታማ የግዥ አፈፃፀም እንዲኖር ጠንክረው መስራት ይገባል ብለዋል ።
በተጨማሪም በግዥ አፈጻጸም መመሪያ እና ደንቦች ይዘት እና የተፈጻሚነት ደረጃን በሚመለከት ግንዛቤ የሰጡ ሲሆን፣ ስለግዥ ዘዴዎች፣ስለመደበኛ የጨረታ ሰነዶች ገለጻ አድርገዋል፡