ቢሮው ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ አካላት በበጀት ዝግጅትና ሂደት ዙሪያ የዜጎች ግንዛቤና ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል ከጂኔላ ወረዳ መስተዳደር ለተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ሰጥቷል።
በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብበር ቢሮ የፋይናንስ ግልፅነትና ተጠያቂት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ኢሊያስ ጂብሪል የስልጠናውን አለማ ሲገልፁ በመንግስት በጀት ሂደት ላይ የዜጎችን ግንዛቤ፣ ተሳትፎና የመረጃ ተደራሽነትን ማሳደግ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ዜጎች በየወረዳቸው በሚኖሩ እንቅስቃሴዎች ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ በቀጣይም የጠያቂነት አቅማቸውን ማዳበር እንዲሁም የመንግስት ተቋማት የግልፅነት አሠራርን እንዲከተሉ ለማድረግ የስልጠና መድረኩ በእጅጉ እንደሚረዳ ተገልጿል፡፡