ከክልል ፓርቲ ጽ/ቤትና በፕላንና ልማት ኮሚሽን የተውጣጡ ቡድኖች የቢሮውን የ2015 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀምን በተጨባጭ ከተከናወኑ ስራዎች አንፃር በጥልቀት የመገምገም ስራ ተከናውኗል ። የምዘና ስርዓት አላማ ተቋማት ያላቸው አፈፃፀም(ውጤታማነት) እየተገመገመ በአፈፃፀማቸው መሰረት ውጤት የሚሰጥና ደረጃዎች የሚቀመጥበት አዲስ አሰራር የሚፈጠር ይሆናል ብለዋል ።
ውጤት ተኮር ምዘናዎች ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር በመሆኑ ትልቁን ድርሻ ይይዛልም ብለዋል ።
በ2015 በጀት አመት የተጀመረው የአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር በሀገራችን የተጀመረውን የለውጥ ሂደት እና የብልፅግና ጉዞ በሁሉም ዘርፍ ከማሳካት አኳያ እና የህብረተሰባችን ጥያቄና ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አኳያ በሁሉም አቅጣጫ ሁሉም ተቋማት የሚመዘኑበትን መሆኑን የምዘና አባላቱ ገልጸዋል። የአገልግሎት አሰጣጥ አፈፃፀም ምዘና ዋንኛ አላማ ተቋሟት ያሉበትን ደረጃ ለመለየት እና በቀጣይ ለሚኖረው የስራ ጊዜ ያሉባቸውን ክፍተቶች በመለየት መሙላት እንደሆነ ተገልጿል ።