የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የተቋቋመበት ተግባርና ኃላፊነት የክልሉን የፋይናንስ ሀብት አጠቃቀም ሥርዓት ውጤታማና ፍትሃዊ በማድረግ የሕዝቡን ቁልፍ ችግሮች በመፍታት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ መነሻ በማድረግ ወደ ትግበራ በመግባት በ2016 በጀት ዓመት የሪፎርም ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ላይ ይገኛል።
ቢሮው የ2016 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸሙን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ መሀመድ ያሕያ መሪነት በበጀትና በጥሬ ገንዘብ አስተዳደር፣ በሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ በውጭ ሃብት ግኝት አጠቃቀምና አፈፃፀም፣በግዥና ንብረት አስተዳደር፣ በውስጥ ኦዲት ቁጥጥር ስርዓትና ግኝት አመላለስ፣ በቴክኖሎጅ አጠቃቀምና በሌሎች ተግባራት የተከናወኑ ስራዎችን በእጥረትና በጥንካሬ በመለየት ገምግሟል።
ከዚህ በተያያዘም በክልላችን የሚመደበውን ውስን ሃብት በወቅቱና በአግባቡ ጠዕቅም ላይ ማዋል፣የኦዲት ግኝትን ተቀናጅቶ ማስመለስ፣የክልሉን የገቢ አቅም ከማሳደግ አንጿር ሃሳብ አንስተው አወያይተዋል።
የክልሉ ገቢና ወጪን በሚመለከት የሀብት አመዳደብ እና አጠቃቀም ውጤታማነትን ከማሻሻል አኳያ ከፌደራል መንግስት የድጎማ፣ከቀጥታ ታክስ፤ ቀጥታ ካልሆኑ ታክስና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን በተመለከተ የተከናወኑ ስራዎችን በስፋት ተዷሳል።
የመንግስት ግዥ አፈፃፀም እና ንብረት አስተዳደር ኦዲት በማከናወን በግኝቶች ላይ እርምት ላይ ክትትል በማድረግ ነቀፌታ ያለበትን የኦዲት ግኝት ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎች ቀርቧል።
ሴክተር መ/ቤቶች ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ ወጪ ማድረግ፤ የተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳብን በመለየት እንዲወራረድ ክትትል ማድረግ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ሆነው ተለይተው ተቀምጠዋል፡፡
በመጨረሻም የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አቶ መሐመድ ያሕያ በጥንካሬ እና በቀጣይ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮችን ላይ አቅጣጫ በመስጠት ግምገማ መድረኩ በጋራ መግባባት ተጠናቋል፡፡