የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ከUNICEF በተገኘ ድጋፍ የተከናወኑ ስራዎችንና አፈፃፀሙን አስመልክቶ ፕሮግራሙን ከሚፈፅሙ ሴክተሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር አፈፃፀሙን ገምግሟል፡፡
በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በበጎ አድራጎት ማህበራት ድርጅት አዘጋጅነት የ2015 በጀት ዓመት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፍ የተከናወኑ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል። በግምገማ መድረኩ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮን የድጋፍና ክትትል ሪፖርት ጨምሮ 2 ቢሮዎች (የጤና ቢሮና ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡ በቀረበው ሪፖርት ላይ በትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችና እቅዶችን ከማስፈጸም አንጻር ስራቸውን በአግባቡ እንዳያከናውኑ ተግዳሮት የሆኑባቸው ጉዳዮች ላይም በስፋት ተወያይተዋል። ተጠያቂነትን ማስፈን ላይ፣ በጀቱን በጊዜ ከማወራረድ አንዷር አፈጻጸም የቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫ ዙሪያ ለውይይቱ ተሳታፊዎች ቀርቦ በመወያየት የአሰራር ማነቆዎችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ጭምር አንስተው መክረዋል፡፡
በመጨረሻም የእርዳታና ብድር ሃብት በተመለከተ አመራሩ እና የዘርፉ ባለሙያዎች በሃላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ ሁሉንም በውጭ ሃብት ፕሮግራሞች የሚመጣውን ሃብት በአግባቡ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ዳይሬክተሬቱ ገልጸዋል፡፡
የ2015 በጀት ዓመት የተባበሩት መንግስታት ፕሮግራሞች እቅድ አፈጻጸም የጋራ ስምምነት የተደረሰባቸውው ጉዳዮች የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡