የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው 6ዙር 2ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ መንግሥት የ2016 በጀት ከ4 ቢሊየን 258 ሚሊየን ብር በላይ አጽድቋል።
የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልባሲጥ አቡበከር ከተያዘው በጀት 58 በመቶ ለካፒታል በጀት እንዲሁም 42 በመቶው ደግሞ ለመደበኛ በጀት የሚውል ነው ብለዋል።
በጀቱም በዋናነት በክልሉ ከተለያዩ ገቢዎች ከሚሰበሰብ ገቢ እና ከፌዴራል መንግስት ድጎማ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል።
የፀደቀው በጀት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ25 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።
የክልሉ ምክር ቤትም በጀቱ ለታለመለት አላማ እንዲውል አቅጣጫ አስቀምጧል።
የክልሉ ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድው የቆየው 6ዙር 2ኛ አመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤ አጠናቋል።