የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በቻናል አንድ ኘሮግራም ለውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች የፋይናንሻል ኦዲት ስልጠና ሰጠ፡፡
የሰልጠናው ኣላማ በውስጥ ኦዲት ሥራ ላይ ላሉ ባለሙያዎች ስለ ውስጥ ኦዲት መሰረተ ሃሳቦች፣ የውስጥ ኦዲት ደረጃዎች፣ የውስጥ ኦዲት የሙያ ሥነ-ምግባር ደንብ፣ እና የፋይናንስ ኦዲት አተገባበር መመሪያ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
አዲተር ለአንድ ተቋም የጀርባ አጥንት እንደሆነና የአዲት ስራ ለመስራት በቂ መረጃና ማስረጃ እንደሚያስፈልግ በመጠቆም አዲተሩ ለተቋሙ አማካሪ መሆኑን በመገንዘብ በዚህ ልክ አስቦ ከሌላው በተሸለ ራሱን ማብቃት አለበት ብለዋል፡፡ የውስጥ ኦዲተሮች በየተቋማቸው የበለጠ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡ በሴክተር መስሪያ ቤቶች አዳዲስ የኦዲት ባለሙያዎች ወደ መዋቅሩ በመካተታቸው የተነሳ እንዲሁም፤ በውስጥ ኦዲት በሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችና ችግሮች፣ በይበልጥም ወደ ፋይናንስ ቢሮ የሚመጡ ሪፖርቶች ጥራት ዝቅተኛ መሆናቸውን ተጠቁሟል፡፡ እነዚህንና ሌሎች ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትና የውስጥ ኦዲተሮቹ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ በቂና ተገቢ የሙያ ድጋፍ በማድረግ በባለበጀት መስሪያቤቶች ውስጥ የሚገኙ ኦዲተሮች የተቋቋሙበትን ዓላማ ከማሳካት አንፃር ውጤታማ ስራ ለመስራት እንዲያስችላቸው በማሰብ ነው ብለዋል፡፡