በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የበጎ አድራጎትና ድርጅቶችና ማህበራት ፕሮጀክቶች ማበልጸግ ክትትልና ግምገማ ዻይሬክቶሬት ኃላፊዎችና ባለሞያዎች ፣የክልልና ወረዳ ፈጻሚዎች በተገኙበት የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ፡፡
አላማውም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ዩኒሴፍ) ድጋፍ የ2013 በጀት ዓመት የተከናዎኑ ፕሮግራሞች አፈጻጸም በመገምገም የቀጣይ ጊዜያት አቅጣጫዎች ለማስቀመጥ ነው፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም በዘርፉ የፕሮግራሙ አስተባባሪ በሆኑት በአቶ መሀመድ ራህመቶ በኩል የቀረበ ሲሆን በትብብር ዘርፉ የታቀፉ የጤና ው(የፖሊዮና ሳኒቴሽን)አፈጻጸም የሚመለከታቸው አካላት ሪፖርታቸውን አቅርበው በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በቀረበው ሪፖርት መሠረትም የውይይቱ ተሳታፊዎች በጥንካሬ እና በድክመት በመለየት አስተያየት እና ጥያቄዎች ተነስተው በዘርፉ በሚመለከታቸው ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች መልስ በመስጠት በሰፊው ተመክሮበት መግባባት ላይ ተደርሶል፡፡
በመጨረሻም ሥራ ተሠርቶ በወቅቱ ሪፖርት አለማድረግ እና በወቅቱ መወራረድ የሚገባውን አለመወራረድ እንደ ተግዳሮት ተነስቷል። በመሆኑም ከዚህ ችግር ወጥተን አፈጻጸማችንን የተሻለ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኝ ሁሉም አካላት ኃላፊነት ወስደን የምንፈጽመው ከመሆኑም ባሻገር እንደዜጋ አደራ አለብን በማለት አስተባባሪው መድረኩን ሲያጠቃልሉ ገልፀዋል፡፡