የቢሮ ኃላፊው አቶ መሀመድ ያህያ በፈርማው ስነ ስርዓት ወቅት ያስተላለፉት መልዕክት በ2016 በጀት ዓመት የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ድክመቶችን በማረም በ2017 በጀት ዓመት ደግሞ የበለጠ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ገልፀው ሁሉም የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለባቸውና ስራን አለቃ አድርጐ መስራት እንደሚጠበቅ ገልፀዋል::
በተጨማሪም ዕቅዱን ወደታች ከማውረድ አንፃር ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች በስራቸው ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር በተመሳሳይ ደረጃ ተፈራርመው ተገቢውን ክትትልና ግምገማ ማድረግ እንደሚገባ ቸው ገልፀዋል፡፡