ጳጉሜን 1 የአገልጋይነት ቀን ኢትዮጵያን እናገልግል በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል፡፡
በማለዳ 1፡00 ሰዓት ላይ በጀመረው የአገልጋይነት ቀን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልባሲጥ ከቢሮው ሰራተኛ ጋር በጋራ በመሆን የጽዳት ዘመቻ ስራ አከናውነዋል።
እለቱ በየተቋሙ ማህበረሰቡን በማገልገል እንደሚከበር የተገለፀ ሲሆን አገልጋይነት ሁሉም ሊላበሰው የሚገባው ባህሪ መሆን አንደሚገባም ተገልጿል ፡፡
የአገልጋይነት ቀን በአንድ ቀን የተገደበ ሳይሆን አመቱን በሙሉ የሚተገበር ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባም ተመላክቷል።
#ማገልገል ክብር ነው!!
# የራስን ህዘብ እና ሀገርን ማገልገል ደግሞ ከክብር ሁሉ የላቀ ክብር ነው